Log in to Faxo
All your favorite apps in oneInvest in Faxo
Continue with Google
Continue with Facebook
Continue with Apple
Use phone, email, or Bluesky
This browser does not support the video element.
ሚዛናዊ አመለካከት/Optimistic/
አመለካከት ማለት የሰው ልጅ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ነው፡፡ የሰው ልጅ የሚያስበው በፅንሰ ሃሳብ ነው፤ የሚያጠነጥነውም በሃሳብ ላይ ሆኖ በዋናነት ችግርን መነሻ በማድረግ የመከላከያ መንገድን በመለየት ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል ነው፡፡ አስተሳሰብም የሚያድገው ውሳኔ ሰጭነታችን እያጠናከርን ስንቀጥልና ገለልተኛ፣ ግልፅ፣ ተመጣጣኝና ተጨባጭ ሲሆን ነው ሚዛናዊ የሚባለው፡፡ ሚዛናዊ አስተሳሰብ በመረጃ የተደገፈና ጥያቄዎቹም በመግባባት፣ በገለፃ ወደ መጨረሻ ውሳኔ የሚደርሱ ናቸው፡፡ ሚዛናዊ አመለካከት ወይም መሠረታዊ አመለካከት ጥንቃቄ የተሞላበት ሆኖ ድምዳሜውም ሁሉንም ተፅዕኖዎችና ተቀባይነት ያላቸውን እውቀቶች ግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ መዳኘት የሚችል ነው፡፡ ምክኒያቱም በመግባባትና ምክንያት ወይም በንግግር፣ በተግባርና በእንቅስቃሴ ይለካል፡፡ ብዙ ጊዜ በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያላቸው እሴቶች ያሉት፣ በድምፅ የሚደገፍ፣ ጥሩ ምክንያት፣ ጥልቅ፣ ሰፊና ፍትሃዊ የሆነ ሃሳብ ነው፡፡ አወቃቀሩ ወይም ስብስቡ ልባዊ የሆነ በሁሉም ምክንያት አላማ ያለው፣ ችግር ወይም ጥያቄ የሚያስነሳ ሃሳብ፣ ተገማች፣ ሂሳባዊ፣ መነሻው ቁጥር አዘል፣ በምክንያት የሚመራና ውጤት የሚሰጥ፣ አማራጭ እይታዎች ያሉት እና መነሻና ማጣቀሻ ያለው ነው፡፡
ሚዛናዊ አመለካከት ሳይንሳዊ አስተሳሰብ፣ ሂሳባዊ አስተሳሰብ፣ ታሪካዊ አስተሳሰብ፣ ማህበረሰባዊ አስተሳሰብ፣ ኢኮኖሚያዊ አስተሳሰብ፣ ሞራላዊ አስተሳሰብ፣ ፍልስፍናዊ አስተሳሰብ ተብለው ሊከፈሉ ይችላሉ፡፡ ሚዛናዊ አስተሳሰብ በሌላ አባባል ኢህጋዊአስተሳሰብ ተብሎ ይጠራል፡፡ ውሳኔው በቁጥር እንዲገለፅ ከተፈለገ ሚዛናዊ አካሄድ ያስፈልጋል፡፡ ሚዛናዊ አስሳሰብ በአካዳሚክ ስራና በስነ ልቦና ዘርፍ ሲታይ በጣም ሰፊ በሰብዓዊነት የሚፈረጅ የሰብዓዊ ሁኔታን የሚያጠና ክፍል ነው፡፡ሚዛናዊ አስተሳሰብ የተለያዩ ኢንፎርሜሽኖችን ለመቆጣጠር እንደ መሳሪያ ይታያል፤ እንደ ስኮሪቨን እና ፓኦል አገላለፅ ሚዛናዊ አስተሳሰብ በአስፈላጊነቱና ተነሳሽነቱ ይለያያል፤ ጥራቱም ባለው አስተሳሰብ ጥልቀትና ጥራት ይለካል።