1. ህይወት አምስት ልጆችን ሰጥታ፤ አይንህን እያየ መልሳ ልትወስዳቸው ትችላለች።

2. እንዲሁም አንድ ልጅ ሰጥታ እርሱ ሲያድግ አንተ አብረህ እንድታረጅ ታደርጋለች።

3. ያችው ህይወት ያለ ልጅ ፣ ጣፋጭ ትዳር ልትሰጥህ ትችላለች።

4. ወይ ደግሞ ትዳር ሳይኖርህ ውብ ልጆችን ልትሰጥህ ትችላለች።

5. አሊያም ደግሞ ያማረ ትዳርና ብዙ ገንዘብ ሰጥታ፤ ነገር ግን ዘወትር የህክምና ክትትል የሚሹ ልጆችን ልትሰጥህ ትችላለች፡፡

6. ያችው ህይወት እጅግ የላቀ የትምህርት ማስረጃ አኑረህ ስራ ልትነሳህ ትችላለች፡፡

7. በሌላ በኩል ደግሞ ምንም ዓይነት የትምህርት ማስረጃ ሳይኖርህ በንግዱ ዓለም ስኬታማ ልታደርግህ ትችላለች።

የሁሉም ሰው የህይወት ጉዞ የተለያየ ነው፡፡ የአንዱ በረከት ለሌላው ፈተና፣ የአንዱ ጉድለት ለሌላው ስጦታ ሊሆን ይችላል። የራስህ ሰዓት እና መድረሻ ከሌሎች የተለየ መሆኑን ተቀበል፡፡

በውጪ ሲታይ የተሟላ የሚመስል ህይወት፤ ውስጥ ለውስጥ የራሱ የሆነ ከባድ ህመም ወይም ጉድለት ሊኖረው ይችላል። ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ የሚሸከመው መስቀል አለው፡፡

ለአንተ ቀላል የሚመስልህ ነገር ( ለምሳሌ ጤና፣ ልጅ፣ ወይም ሰላም) ለሌላው ሰው የህይወት ዘመን ህልሙ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ በተሰጠህ ነገር መደሰትን ተለማመድ፡፡ ትምህርት፣ ጋብቻ፣ ወይም ልጅ መውለድ ብቻቸውን የደስታ ወይም የስኬት መለኪያዎች አይደሉም፡፡ ህይወት ለእያንዳንዱ ሰው የተለያየ የስኬት መንገድ አዘጋጅታለች፡፡

አንድ ሰው ስላለው ነገር ወይም ስለሌለው ነገር _ አትፍረድበት። ከአንተ እይታ በስተጀርባ ህይወት ያሰመረችለት ወይም የነሳችው ነገርምን እንደሆነ አታውቅምና፡፡

አንድ ነገር ግን ልብ በሉ በዚህ አለም እድል እንዳለ ሆኖ ህይወታችን በአብዛኛው ጥሩ እንዲሆን እና መጥፎ እንዲሆን የምናደርገው በራሳችን ውሳኔ ነው። እናስብ ፣ እናድርገው ፣ እየተደሰትን እንኑርበት። ስለዚ እናስተውል።

ከቲክቶክ መንደር ያገኘሁት ከተማራችሁበት ላይክ 👍

  Hong Zigzagi43


Apps
About Faxo